የዝምታ እሪታ! ዝምያለ በመሰለው የዙሪያው ፀጥታ ባንሰማው ነው እንጅ አለ ብዙ እሪታ! አፉም ባይከፈት - ምላስ ባይናገር ድምፁ ባይሰማም - ምንም ባይፈጠር ከውስጡ የሚጮህ አለ ብዙ ነገር፡፡ በዝምታው መሀል ድምፅ በሌለበት ከሚንቀሳቀሱት ሰውና ፍጥረታት ኮሽታም በሌለው ወፍ በማይዞርበት ባንሰማው ነው እንጅ አለ ብዙ ጩኸት! ፀጥ እረጭ ብሎ ሰላም በመሰለው ከዚህ ውስጥ ሁኖ ከሚብሰለሰለው ልውጣ አልውጣ እያለ ከሚንተከተከው ገፍቶ አልወጣም እንጅ ዝምታም ጩኸት ነው! ዝምብሎ ቢቀመጥ ሁሉም በፀጥታ ምንም ባይናገር በያለበት ቦታ ከውስጥ ላይ ያለው ጩኸትና ዋይታ ታፍኖ ነው እንጅ ታስሮ በዝምታ ድብልቅልቅ ያለነው እሪታ! በእሪታ! ከተጠላለፈው የነገር ጋጋታ አዳፍኖ ከያዘው የውስጡ ቅሬታ ሁሉም ውሉ ጠፍቶ አንዱም ባይፈታ ከውስጥ ያስተጋባል የዝምታ እሪታ!!
ይህ ገፅ የተለያዮ ቁምነገር አዘልና ሀገራዊ ጉዳዮች የሚተላለፋበትና አስተያየቶች የሚስተናገዱበት ገፅ ነው፡፡