ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የአፄ ፋሲል ግንብ - ጎንደር


የአፄ ፋሲል ግንብ - ጎንደር

የአፄ ፋሲል ግንብ የተገነባው በአፄ ፋሲለደስ ዘመነ መንግስት በ 1632 ዓመተ ምህረት ነው፡፡ በአጠቃላይ ስፋቱ 70,000 ካሬ ሜትር ሲሆን አስራሁለት በሮች አሉት፡፡ የበሮቹ ስምም፡- አንኮየ በር፣ እርግብ በር፣ ባልደራስ በር፣ ወንበር በር፣ ኳሊ በር፣ ራስ በር፣ ፊት በር፣ ግምጃቤት ማርያም በር፣ አዛዥ ጠቋሬ በር፣ አደናግር በር፣ እምቢልታ በርና እልፍኝ በር ይባላሉ፡፡
በአፄ ፋሲል ግንብ ውስጥ የስድስት ነገስታት ቤተ-መንግስት ይገኛል፡፡ እነዚህም አፄ ዮሀንስ፣ አድያምሰገድ እያሱ፣ አፄ በካፋ፣ ቋረኛው እያሱ፣ አፄ ፋሲለደስና እትየ ምንትዋብ ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ "The Camelot of Africa" "የአፍሪካ ቤተ-መንግስት" እየተባለም ይጠራል፡፡ በድርቡሾች ወረራና በእንግሊዞች የአውሮፕላን ጥቃት ደርሶበታል፡፡ በዓለም ቅርስነት በዮኔስኮ የተመዘገበው በ 1979 ዓ.ም ነው፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ትዝታ ነሽ ለ'ኔ

አፄ ቴዎድሮስ

ስለ አፄ ቴዎድሮስ ከተባሉት...