አፄ ቴዎድሮስ
አፄ ቴዎድሮስ ከሚታወቁበት ጀግንነት፣ ብልህና አስተዋይ ሀገር ወዳድነታቸው በተጨማሪ የስነ-ፅሁፍ ችሎታም እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል፡፡ ይህን በተመለከተም በአንድ ወቅት በጣም ይወዷት የነበረችው ባለቤታቸው እትየ ተዋበችን በሞት እንደተነጠቁ ውስጣቸው በከባድ ሀዘን ይሰበራል፡፡ ከዚያም ለንጉስ በሚደረገው ስነ-ስርዓት መሰረት ተዘጋጅቶ ህዝቡ በሙሉ ወጥቶ የእቴጌይቱን አስከሬን አጅቦ ወደ ቀብር ቦታ እየተጓዘ እያለ አፄ ቴዎድሮስ ሀዘናቸውን ለመግለፅ እንዲህ ብለው አስገጠሙ፡-
"እስኪ ጠይቁልኝ እርቃ ሳትሄድ
እትየ ተዋበች ሚስትናት ገረድ"
ከዚህ ግጥም ላይ ሰሙና ወርቁን በተመለከተ ያለው ከሁለተኛው ስንኝ ላይ ሲሆን - ሰሙ "ሚስት ናት ገረድ" የሚል ሲሆን፤ ወርቁ ደግሞ "ሚስት፣ እናት፣ ገረድ" የሚል ይዘት ያለው ሆኖ እትየ ተዋበች ሚስቴም፣ እናቴም ገረዴም ነበረች ለማለት ነው፡፡
አስተያየቶች