ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

"አያሌው ሞኙ..."

"አያሌው ሞኙ...." "አያሌው ሞኙ..." "አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ" "አያል ባያል ስራው በአል.." ከላይ የተገለፁትን የባህል ዘፈኖች ብዙ ጊዜ ሲባሉና ሲዘፈኑ ሰምተናቸው የምናውቅ ሰዎች የእነዚህ ዘፈኖችና ስንኞች ታሪካዊ አመጣጥ ምን እንደሆነ ስንቶቻችን ነው የምናውቀው? ይህን በተመለከተም ትክክለኛው የታሪኩ አመጣጥ ከዚህ በታች የተዘረዘረው እውነተኛው የታሪኩ አጋጣሚ ነው፡፡ የዚህ ታሪክ ዋነኛ መነሻ የሆኑት ደጃች አያሌው ብሩና ራስ ጉግሳ ወሌ ሲሆኑ፤ ደጅአዝማች አያሌው በንጉሱ ጊዜ የሰሜን በጌምድር ማለትም ወገራ፣ ዳባትና ደባርቅ ገዥ ነበሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ራስ ጉግሳ የደጅአዝማች አያሌው ወንድም ናቸው፡፡ አፄ ኃ/ስላሴ ራስ ጉግሳን በተደጋጋሚ ወደ አዲስአበባ እንዲመጡ ቢልኩባቸውም ራስ ጉግሳ እራሳቸው የንግስናውን ወንበር ይፈልጉት ስለነበር የንጉሱን ጥሪ ሳይቀበሉ አሻፈረኝ ብለው ቀሩ፡፡ በዚያን ወቅት ንጉስ እንዲመጣ ልኮበት የቀረ ሰው እንደሸፀተ ይቆጠር ስለነበር አፄ ኃ/ስላሴን ነገሩ በጣም አበሳጫቸው በጣምም አሳሰባቸው፡፡ ከዚያም ወንድማቸውን ደጅአዝማች አያሌውን ይጠሩና ወንድምህ ራስ ጉግሳ እንዲመጣ ደጋግሜ ብልክበትም አሻፈረኝ ብሎ ሳይመጣ ቀረ፡፡ ስለዚህ አንተ ሂድና ከቻልክ እጁን ይዘህ ካለያ ገለህ ከመጣህ አሁን ከያዝከው ግዛት በተጨማሪ ሌላ ግዛት እጨምርሃለው አሉአቸው፡ ደጃች አያሌውም በተገባላቸው የግዛት እጨምርሃለው ተስፋ ተታለው ትልቅ ወንድማቸውን ሊወጉ ጦርአቸውን አዘጋጅተው በወሎ በኩል አድርገው ይሄድና አንችም ከሚባለው ቦታ ላይ ትልቅ ወንድማቸውን ገጥመው ገደሉአቸው፡፡ ከዚያ ወደ ኃ/ስላሴ ተመልሰው የተባሉትን ፈፅመው ስለመጡ ቃል የተገባላቸውን ግዛት እንዲጨምሩላቸው ...

የዝምታ እሪታ!

የዝምታ እሪታ! ዝምያለ በመሰለው የዙሪያው ፀጥታ ባንሰማው ነው እንጅ አለ ብዙ እሪታ! አፉም ባይከፈት - ምላስ ባይናገር ድምፁ ባይሰማም - ምንም ባይፈጠር ከውስጡ የሚጮህ አለ ብዙ ነገር፡፡ በዝምታው መሀል ድምፅ በሌለበት ከሚንቀሳቀሱት ሰውና ፍጥረታት ኮሽታም በሌለው ወፍ በማይዞርበት ባንሰማው ነው እንጅ አለ ብዙ ጩኸት! ፀጥ እረጭ ብሎ ሰላም በመሰለው ከዚህ ውስጥ ሁኖ ከሚብሰለሰለው ልውጣ አልውጣ እያለ ከሚንተከተከው ገፍቶ አልወጣም እንጅ ዝምታም ጩኸት ነው! ዝምብሎ ቢቀመጥ ሁሉም በፀጥታ ምንም ባይናገር በያለበት ቦታ ከውስጥ ላይ ያለው ጩኸትና ዋይታ ታፍኖ ነው እንጅ ታስሮ በዝምታ ድብልቅልቅ ያለነው እሪታ! በእሪታ! ከተጠላለፈው የነገር ጋጋታ አዳፍኖ ከያዘው የውስጡ ቅሬታ ሁሉም ውሉ ጠፍቶ አንዱም ባይፈታ ከውስጥ ያስተጋባል የዝምታ እሪታ!!

እያለን የለንም!

እያለን የለንም! ሁሌ በየዕለቱ እንደተገናኘን መልካችን እያየን አንዳችን ያንዳችን እንዴት ነው? ስንባል አለን! እንላለን ላይ ላዩን ለይምሰል ትንሽ ፈገግ ብለን፡፡ አለን! አለን! እያልን - ያለን ቢመስለንም መኖራችን እንጅ - እያለን የለንም!!

የአፄ ፋሲል ግንብ - ጎንደር

የአፄ ፋሲል ግንብ - ጎንደር የአፄ ፋሲል ግንብ የተገነባው በአፄ ፋሲለደስ ዘመነ መንግስት በ 1632 ዓመተ ምህረት ነው፡፡ በአጠቃላይ ስፋቱ 70,000 ካሬ ሜትር ሲሆን አስራሁለት በሮች አሉት፡፡ የበሮቹ ስምም፡- አንኮየ በር፣ እርግብ በር፣ ባልደራስ በር፣ ወንበር በር፣ ኳሊ በር፣ ራስ በር፣ ፊት በር፣ ግምጃቤት ማርያም በር፣ አዛዥ ጠቋሬ በር፣ አደናግር በር፣ እምቢልታ በርና እልፍኝ በር ይባላሉ፡፡ በአፄ ፋሲል ግንብ ውስጥ የስድስት ነገስታት ቤተ-መንግስት ይገኛል፡፡ እነዚህም አፄ ዮሀንስ፣ አድያምሰገድ እያሱ፣ አፄ በካፋ፣ ቋረኛው እያሱ፣ አፄ ፋሲለደስና እትየ ምንትዋብ ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ "The Camelot of Africa" "የአፍሪካ ቤተ-መንግስት" እየተባለም ይጠራል፡፡ በድርቡሾች ወረራና በእንግሊዞች የአውሮፕላን ጥቃት ደርሶበታል፡፡ በዓለም ቅርስነት በዮኔስኮ የተመዘገበው በ 1979 ዓ.ም ነው፡፡

"አያሌው ሞኙ...."

"አያሌው ሞኙ..." "አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ" "አያል ባያል ስራው በአል.." ከላይ የተገለፁትን የባህል ዘፈኖች ብዙ ጊዜ ሲባሉና ሲዘፈኑ ሰምተናቸው የምናውቅ ሰዎች የእነዚህ ዘፈኖችና ስንኞች ታሪካዊ አመጣጥ ምን እንደሆነ ስንቶቻችን ነው የምናውቀው? ይህን በተመለከተም ትክክለኛው የታሪኩ አመጣጥ ከዚህ በታች የተዘረዘረው እውነተኛው የታሪኩ አጋጣሚ ነው፡፡ የዚህ ታሪክ ዋነኛ መነሻ የሆኑት ደጃች አያሌው ብሩና ራስ ጉግሳ ወሌ ሲሆኑ፤ ደጅአዝማች አያሌው በንጉሱ ጊዜ የሰሜን በጌምድር ማለትም ወገራ፣ ዳባትና ደባርቅ ገዥ ነበሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ራስ ጉግሳ የደጅአዝማች አያሌው ወንድም ናቸው፡፡ አፄ ኃ/ስላሴ ራስ ጉግሳን በተደጋጋሚ ወደ አዲስአበባ እንዲመጡ ቢልኩባቸውም ራስ ጉግሳ እራሳቸው የንግስናውን ወንበር ይፈልጉት ስለነበር የንጉሱን ጥሪ ሳይቀበሉ አሻፈረኝ ብለው ቀሩ፡፡ በዚያን ወቅት ንጉስ እንዲመጣ ልኮበት የቀረ ሰው እንደሸፀተ ይቆጠር ስለነበር አፄ ኃ/ስላሴን ነገሩ በጣም አበሳጫቸው በጣምም አሳሰባቸው፡፡ ከዚያም ወንድማቸውን ደጅአዝማች አያሌውን ይጠሩና ወንድምህ ራስ ጉግሳ እንዲመጣ ደጋግሜ ብልክበትም አሻፈረኝ ብሎ ሳይመጣ ቀረ፡፡ ስለዚህ አንተ ሂድና ከቻልክ እጁን ይዘህ ካለያ ገለህ ከመጣህ አሁን ከያዝከው ግዛት በተጨማሪ ሌላ ግዛት እጨምርሃለው አሉአቸው፡ ደጃች አያሌውም በተገባላቸው የግዛት እጨምርሃለው ተስፋ ተታለው ትልቅ ወንድማቸውን ሊወጉ ጦርአቸውን አዘጋጅተው በወሎ በኩል አድርገው ይሄድና አንችም ከሚባለው ቦታ ላይ ትልቅ ወንድማቸውን ገጥመው ገደሉአቸው፡፡ ከዚያ ወደ ኃ/ስላሴ ተመልሰው የተባሉትን ፈፅመው ስለመጡ ቃል የተገባላቸውን ግዛት እንዲጨምሩላቸው ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ነገርግን ንጉሱ በቃ...

አፄ ቴዎድሮስ

አፄ ቴዎድሮስ አፄ ቴዎድሮስ ከሚታወቁበት ጀግንነት፣ ብልህና አስተዋይ ሀገር ወዳድነታቸው በተጨማሪ የስነ-ፅሁፍ ችሎታም እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል፡፡ ይህን በተመለከተም በአንድ ወቅት በጣም ይወዷት የነበረችው ባለቤታቸው እትየ ተዋበችን በሞት እንደተነጠቁ ውስጣቸው በከባድ ሀዘን ይሰበራል፡፡ ከዚያም ለንጉስ በሚደረገው ስነ-ስርዓት መሰረት ተዘጋጅቶ ህዝቡ በሙሉ ወጥቶ የእቴጌይቱን አስከሬን አጅቦ ወደ ቀብር ቦታ እየተጓዘ እያለ አፄ ቴዎድሮስ ሀዘናቸውን ለመግለፅ እንዲህ ብለው አስገጠሙ፡- "እስኪ ጠይቁልኝ እርቃ ሳትሄድ እትየ ተዋበች ሚስትናት ገረድ" ከዚህ ግጥም ላይ ሰሙና ወርቁን በተመለከተ ያለው ከሁለተኛው ስንኝ ላይ ሲሆን - ሰሙ "ሚስት ናት ገረድ" የሚል ሲሆን፤ ወርቁ ደግሞ "ሚስት፣ እናት፣ ገረድ" የሚል ይዘት ያለው ሆኖ እትየ ተዋበች ሚስቴም፣ እናቴም ገረዴም ነበረች ለማለት ነው፡፡

ስለ አፄ ቴዎድሮስ ከተባሉት...

ትንሽ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ጀግንነትን በተመለከተ ከተፃፋና ከተባለላቸው በጥቂቱ፡- ".... አንች እማማ ኢትዮጲያ - ሰማሽ አንች እናትዓለም ቃል የእምነት ዕዳ እንጅ የእናት አባት እኮ አይደለም፡፡ እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ እጅ ተይዞ ሊወሰድ ምን እጅ አለኝ የሳት ቃጠሎ የሳት ነደድ አያውቅም እንዴ ክንዴ እንደሚያነድ...." "መቅደላ አፋፋ ላይ ጬኸት በረከተ የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ" "ገደልን እንዳይሉ ሙተው አገኙአቸው ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው ምን አሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው ለወሬ አይመቹም ተንኮለኛ ናቸው"