ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

"አያሌው ሞኙ...."

"አያሌው ሞኙ..."

"አያሌው ሞኙ
ሰው አማኙ"
"አያል ባያል
ስራው በአል.."

ከላይ የተገለፁትን የባህል ዘፈኖች ብዙ ጊዜ ሲባሉና ሲዘፈኑ ሰምተናቸው የምናውቅ ሰዎች የእነዚህ ዘፈኖችና ስንኞች ታሪካዊ አመጣጥ ምን እንደሆነ ስንቶቻችን ነው የምናውቀው? ይህን በተመለከተም ትክክለኛው የታሪኩ አመጣጥ ከዚህ በታች የተዘረዘረው እውነተኛው የታሪኩ አጋጣሚ ነው፡፡
የዚህ ታሪክ ዋነኛ መነሻ የሆኑት ደጃች አያሌው ብሩና ራስ ጉግሳ ወሌ ሲሆኑ፤ ደጅአዝማች አያሌው በንጉሱ ጊዜ የሰሜን በጌምድር ማለትም ወገራ፣ ዳባትና ደባርቅ ገዥ ነበሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ራስ ጉግሳ የደጅአዝማች አያሌው ወንድም ናቸው፡፡
አፄ ኃ/ስላሴ ራስ ጉግሳን በተደጋጋሚ ወደ አዲስአበባ እንዲመጡ ቢልኩባቸውም ራስ ጉግሳ እራሳቸው የንግስናውን ወንበር ይፈልጉት ስለነበር የንጉሱን ጥሪ ሳይቀበሉ አሻፈረኝ ብለው ቀሩ፡፡ በዚያን ወቅት ንጉስ እንዲመጣ ልኮበት የቀረ ሰው እንደሸፀተ ይቆጠር ስለነበር አፄ ኃ/ስላሴን ነገሩ በጣም አበሳጫቸው በጣምም አሳሰባቸው፡፡ ከዚያም ወንድማቸውን ደጅአዝማች አያሌውን ይጠሩና ወንድምህ ራስ ጉግሳ እንዲመጣ ደጋግሜ ብልክበትም አሻፈረኝ ብሎ ሳይመጣ ቀረ፡፡ ስለዚህ አንተ ሂድና ከቻልክ እጁን ይዘህ ካለያ ገለህ ከመጣህ አሁን ከያዝከው ግዛት በተጨማሪ ሌላ ግዛት እጨምርሃለው አሉአቸው፡ ደጃች አያሌውም በተገባላቸው የግዛት እጨምርሃለው ተስፋ ተታለው ትልቅ ወንድማቸውን ሊወጉ ጦርአቸውን አዘጋጅተው በወሎ በኩል አድርገው ይሄድና አንችም ከሚባለው ቦታ ላይ ትልቅ ወንድማቸውን ገጥመው ገደሉአቸው፡፡ ከዚያ ወደ ኃ/ስላሴ ተመልሰው የተባሉትን ፈፅመው ስለመጡ ቃል የተገባላቸውን ግዛት እንዲጨምሩላቸው ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ነገርግን ንጉሱ በቃላቸው መሰረት የተባለውን ግዛት ሳይጨምሩላቸው ነገ ዛሬ እያሉ ሲያመላልሱአቸው ቆዩ፡፡ በዚህ መሀል የወገራና የዳባት እረኛ በደጅአዝማች አያሌው መታለል ሲቀልዱባቸው፡- "አያሌው ሞኙ
              ሰው አማኙ..."
ብለው ተዘባበቱባቸው፡፡
ደጃች አያሌውም በመጨረሻ በንዴት ብዛት የተነሳ ውስጣቸው በጣም ስለተጎዳ በከፍተኛ ሁኔታ ታመው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተኝተው ሲታከሙ ቆይተው እንደሞቱ ይነገራል፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የአፄ ፋሲል ግንብ - ጎንደር

ትዝታ ነሽ ለ'ኔ

አፄ ቴዎድሮስ

ስለ አፄ ቴዎድሮስ ከተባሉት...