ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ, 2017 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ስለ አፄ ቴዎድሮስ ከተባሉት...

ትንሽ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ጀግንነትን በተመለከተ ከተፃፋና ከተባለላቸው በጥቂቱ፡- ".... አንች እማማ ኢትዮጲያ - ሰማሽ አንች እናትዓለም ቃል የእምነት ዕዳ እንጅ የእናት አባት እኮ አይደለም፡፡ እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ እጅ ተይዞ ሊወሰድ ምን እጅ አለኝ የሳት ቃጠሎ የሳት ነደድ አያውቅም እንዴ ክንዴ እንደሚያነድ...." "መቅደላ አፋፋ ላይ ጬኸት በረከተ የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ" "ገደልን እንዳይሉ ሙተው አገኙአቸው ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው ምን አሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው ለወሬ አይመቹም ተንኮለኛ ናቸው"

የመጨረሻው መጀመሪያ

የመጨረሻው መጀመሪያ ሁሉም እያለቀ - ሲሄድ እያበቃ ማሰሪያው ሲላላ - ግድግዳው ሲነቃ እንደ መጀመሪያው አልሆን ሲል ነገሩ የቀረበው ሲርቅ - ሲረዝም አጭሩ ይህን ላስተዋለው - ነገሩ ለገባው የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ነው፡፡

የሰው ህዋስ...

የሰው ህዋስ... አንድ ነጠላ የሰው ህዋስ የአንድ ኢንች 1/1000 የሚመጥን እያንዳንዳቸው ስድስት መቶ ገጾች ያልዋቸው፣ ከአንድ ሽህ መፅሀፍ በላይ ሊሞሉ የሚችሉ መመሪያዎች ወይም ትዕዛዞችን በዲ.ኤን.ኤ ውስጥ ይዞ ማስተላለፍ ይችላል፡፡ ምንጭ - የአሁኑነት ሀይል ከሚለው የትርጉም መፅሀፍ

የደስተኝነት ሚስጥሩ...

የደስተኝነት ሚስጥሩ ያለው አንጎላችን ውስጥ ነው አንጎላችን ኒውሮትራንስሚተርስ በሚባሉ ኬሚካሎችና በሌሎች ለአዕምሮአችን ምግብና መከላከያ በሚያገለግሉ ውህዶች የተሞላ ነው፡፡ አንጎላችን ብቻውን የተገነባው መቶ ቢሊዬን በሚጠጉ የነርብ ህዋሳት ነው፡፡ የደስተኝነት ሚስጥሩ ያለው አንጎላችን ውስጥ ነው፡፡ አዲስ ነገርን ሲቃኙ የሚነቃቁት የአንጎላችን ሪሲፕተሮች በባህሪው ኢንዶርፊንስና ዶፖሚን፣ ሲሮቶኒን የተሰኙ ኬሚካሎችን ያፈልቃሉ፡፡ እነዚህ የአንጎላችን የውስጥ ቅመሞች ሲፈልቁ ደስተኛ መሆን ይጀመራል፡፡ ኒኩለስ አኩውመንስ የአንጎላችን የውስጠኛ ክፍል ነው፡፡ በሴንሴሪ ኮርቴክስና በአምስቱ የስሜት ህዋሳት አማካኝነት ይሰራል፡፡ ምንጭ - The Mind (በዶ/ር አቡሽ)

የደስተኝነት ሚስጥሩ...

የደስተኝነት ሚስጥሩ ያለው አንጎላችን ውስጥ ነው አንጎላችን ኒውሮትራንስሚተርስ በሚባሉ ኬሚካሎችና በሌሎች ለአዕምሮአችን ምግብና መከላከያ በሚያገለግሉ ውህዶች የተሞላ ነው፡፡ አንጎላችን ብቻውን የተገነባው መቶ ቢሊዬን በሚጠጉ የነርብ ህዋሳት ነው፡፡ የደስተኝነት ሚስጥሩ ያለው አንጎላችን ውስጥ ነው፡፡ አዲስ ነገርን ሲቃኙ የሚነቃቁት የአንጎላችን ሪሲፕተሮች በባህሪው ኢንዶርፊንስና ዶፖሚን፣ ሲሮቶኒን የተሰኙ ኬሚካሎችን ያፈልቃሉ፡፡ እነዚህ የአንጎላችን የውስጥ ቅመሞች ሲፈልቁ ደስተኛ መሆን ይጀመራል፡፡ ኒኩለስ አኩውመንስ የአንጎላችን የውስጠኛ ክፍል ነው፡፡ በሴንሴሪ ኮርቴክስና በአምስቱ የስሜት ህዋሳት አማካኝነት ይሰራል፡፡ ምንጭ - The Mind (በዶ/ር አቡሽ)

In the Unitedstates...

In the Unitedstates... Every night in the Unitedstates morethan six million sleeping tabletes are required to put the American people to sleep. American people are using about twelve million doses of sleeping tabletes perday. In the Unitedstates there was a total of seven and a half billion headaches. This works itself out at approximately fifty headaches per head per annum. Source - Purpose driven life          By Rick Warren

ትዝታ ነሽ ለ'ኔ

ትዝታ ነሽ ለ'ኔ ጎሃ ካናቱ ላይ - ከኮረብታው ቆሜ ቁልቁል ስማትርሽ የቆንጆ ልጅና - ያ'በባ መዓዛ ሲፈልቅ በጎዳናሽ ካ'ዘዞ ቸቸላ - ከፒያሳ እንብርትሽ...እስከ አሸዋሜዳ ...ከብልኮ ጥጉ - ወዲህ እስከ አራዳ አየሁ አንች ምድር!... ውበትና ታሪክ - ከምድርሽ ሲመነጭ አንድነት ሲቀዳ፡፡ ምስጢር ነው ውበትሽ - ሲርቁት ይጠብቃል ባ'መድ ማህፀን ውስጥ - ራሱን ሸሽጎ - እንደሚግም እሳት ከውስጤ ተቀብሮ - ፈጀኝ ረመጡ - ጠበሰኝ መለየት፡፡ እርግጥ ደሮ ማታ - ላንድ ቀን ስንብት..ፍርሃትን ብኖርም ደርዘን ወራት ሙሉ - መራገድን አርግዤ..ሀሳብን ባምጥም ጣር ጥፍሮቹን ስሎ - መውጊያ ጦሩን ይዞ..በግንባሬ ቢቆም መለየት አድብቶ - ጥላዮን ተጋርቶ..ስር ስሬን ቢከርምም ዛሬ ከኔ ሸሽታ!! መጥለም - መጥለቋን ግን.. እንዲህ አልጠበኩም፡፡ የምንትዋብ ማተብ - የታሪክ እመቤት..የቴዎድሮስ ፍቅሩ ጎንደር አባ ጃሌ - የዞብል መስገሪያ.. የፋሲል መንበሩ የሰቀዘኝ ውጋት - የመለየት ጦሩ..ቀለል እንኳን ቢለኝ ስስት አትሁኝብኝ - እንደምንም ብለሽ..አስኮርፈሽ ላኪኝ፡፡ የሀይማኖት ደብር የሊቃውንት አገር የነገስታት ምድር የታሪክ መዘክር ትዝታ ነሽ ለ'ኔ ትዝታ ነሽ ጎንደር፡፡ (ከረዘመ ትንፋሽ መድብል)

Take time..,

Take Time... - Take time to lough - It is the music of soul. - Take time to think - It is the source of power. - Take time to play - It is the source of perpetual youth. - Take time to read - It is the fountain of wisdom. - Take time to love and beloved - It is a God-given privilege. - Take time to be friendly - It is the road to happiness. - Take time to give - It is too short a day to be selfish. - Take time to work - It is the price of success. Source - Courage and confidence          By Norman Vincent

የሰውነት አካሎቻችንና የህይዎት ሞገድ አፈጣጠር

የሰውነት አካሎቻችንና የህይዎት ሞገድ አፈጣጠር ሰው ፈጣን ሽክርክሪት ያላቸው ሞሎኪውሎች ክምችት ነው፡፡ የሞሎኪውሎቹ የማያቋርጥ እንቅስቃሴ የኤሌክትሪክ ፀባይ ያመነጫል፡፡ ይህ የኤለክትሪክ ሞገድ ከእኛ በላይ ስብዕና ከሚለካው ኤሌክትሪክ ሞገድ ጋር በአንድነት በመግጠም የህይወት ሞገድን ይፈጥራል፡፡ ቁስአካላዊነት የጅኖቻችን መስራች አካላት ሞሎኪውሎች ናቸዉ፡፡ ሞሎኪውሎች ደግሞ የተፈጠሩት ከአተሞች ነው፡፡ እያንዳንዳቸው የሰውነት ክፍሎቻችንም ከጅኖች በተገኙ የፕሮቲን ሞሎኪውሎች የተገነቡ ናቸው፡፡ ኢነርጂው ከፈጠራቸው ነገሮቻችን ውስጥ የሰውነት አካሎቻችን ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ኢነርጂ አሁን የያዝነውን አካል እንዲፈጠር ያደረገው በቅድሚያ ህብለ ንድፈ በራሂ ዘሮችን ፈጥሮ ነው፡፡ ህብለ ንድፈ ዘሮቾ ጅኖች ናቸው፡፡ ከጅኖች ቅንብር የተሰሩት ደግሞ ዲ.ኤን.ኤዎች ናቸው ወይም አር.ኤን.ኤ የሚባሉ ሞሎኪውሎች ናቸው፡፡ ዲ.ኤን.ኤዎች በሌላ ቋንቋ ክሮሞዞሞች ይባላሉ፡፡ በሰዎችም ላይ 23 ጥንድ ክሮሞዞሞች አሉ፡፡ ክሮሞዞሞች ወይም ዲ.ኤን.ኤዎች ወይም ጅኖች ከተለያዮ አተሞች የተቀናበሩ ሞሎኪውሎች ናቸው፡፡ ነገርግን ተራ ሞሎኪውሎች አይደሉም፡፡ በውስጣቸው ብዙ መረጃዎችን የያዙ ናቸው፡፡ /ይህን ያገኙት ሳይንቲስቶች ዋትሰንና ክሪክ ይባላሉ፡፡/ እያንዳንዳችን ስንፀነስ 23 ነጠላ ክሮሞዞሞችን ከአባታችን 23 ነጠላ ክሮሞዞሞች ከእናታችን ተዋህደው ነው 23 ጥንድ ክሮሞዞሞችን የያዝነውን እኛን ያስገኙት፡፡

እግዚአቤርን ለመግለፅ....

እግዚያቤርን ለመግለፅ ሦስት ቃላትን እንጠቀማለን፡፡ የመጀመሪያው እግዚያብሄር ሁሉን አዋቂ (Omniscient) ነው የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው የትም ቦታ የሚገኝ (Omnipresent) ነው፡፡ ሦስተኛው ምንም የማይሳነው (Omnipotent) የሚል ነው፡፡

Intelligent Quotient (IQ)

Intelligent Quotient(IQ) /ሚዛነ ማዕምር የሰውን ልጅ የማሰብ አቅም (ችሎታ) ወይም Intelligent Quotient (IQ) ለመለካት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አራት መለኪያዎች ያስፈልጋሉ አነሱም - - የአንድ ሰው የመፍጠር ችሎታውን - የአመንክዮ ክህሎቱን /የማሳመን/ - የማገናዘብና የመመርመር አቅሙን - የማያወላውል ውሳኔ የመወሰን ጥንካሬውን የሚመረምሩ መጠይቆች ናቸው፡፡ ቀመሩም -  Intelligent Quotient = Mental age/chronological age × 100 ሚዛነ ማዕምር = እድሜ አዕምሮ/እድሜ ሰብዕ × 100 በዚህ መሰረት ከዘጠና አስከ መቶ አስራ አምስት አካባቢ ሚዛነ ማዕምር ያላቸው ናቸው ጤነኛ ወይም አማካይ አስተሳሰብ አላቸው ተብሎ የሚገመተው፡፡ እስካሁን የሰውን ልጅ የማሰብ አቅምን ከፍ ለማድረግ ተብለው ከተመረቱ መድሀኒቶች ውስጥ ጊንሳባይሎባና ሞዳፊኒል የሚባሉት ይጠቀሳሉ፡፡

3ኛው ዳይሜንሽን ምንድን ነው?

3ኛው ዳይሜንሽን ምንድን ነው? ኳንተም ፊዚክስ መላው ዮንበርስንና በዮንበርስ ውስጥ ያሉትን ነገሮች በሙሉ የሚታዮትንም ሆነ የማይታዮትን ከምን ለምንና እንዴት እንደተሰሩ የሚያጠናና የሚያጠነጥን የፊዚክስ ዘርፍ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ይህ ዓለም ያለው በሶስተኛው ዳይሜንሽን ውስጥ ነው፡፡ ዮንበርሳችን አስራአንድ ዳይሜንሽኖች አሉት፡፡ እኛ ያለንባትና የምንኖርባት ዓለም ህይወት ነገሮችን መቃኘት የምትችለው ወደ ጎን እርዝማኔን፣ ወደ ላይ ቁመትንና ወደ ውስጥ ጥልቀትን ብቻ በመሆኑ ነው 3ኛው ዳይሜንሽን የምንባለው፡፡ ከዚህ ውጭ ማየትና መቃኘት ቢቻልም ለሁላችንም ግን አይደለም፡፡ ወደ አራተኛው ዳይሜንሽን መግባት ያስፈልጋል፡፡

ከለር (ቀለም) ምንድን ነው?

ሞገዶች የሚለኩት በፍሪኩዌንሲ ነው፡፡ ፍሪኩዌንሲ ማለት በአንድ ሰከንድ ውስጥ የሚደረግ የሞገድ ድግግሞሽ ነው፡፡ አንዱ ኢነርጂ ከሌላው የሚለየው በኢነርጂ ሞገዱ መጠን ነው፡፡ እያንዳንዱ ነገር በሚኖረው የሞገድ ወይም የፍሪኩዌንሲ ልክ ሊታይና ሊጨበጥ፣ ሊዳሰስ፣ ሊሸተትና ሊቀመስ ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ ተቃራኒውን ባህሪያት ሊይዝና ነገርየው የህዋ ባህሪን ሊጋራ ይችላል፡፡ የፀሀይ ብርሃን ጨረሮች ሲፈጠሩ ተቀልመው አልተፈጠሩም፤ ቀለሙን የፈጠረው የጨረሮች የፍሪኩዌንሲ ስብጥር ነው፡፡ የሚታዮ የብርሃን ጨረሮች (ቀለም ያላቸው) እንዳሉ ሁሉ የማይታዮ ጨረሮችም አሉ፡፡ በእርግጥ የብርሃን ጨረሮቹ ያልታዮት ፍሪኩዌንሳኀው ከፍተኛ በመሆኑና አንጎላችንም በከለር መልክ ለመሳል አቅም ስሌለው ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ገሀድ ዓለም የሃይል ፍሪኩዌንሲ እንጅ ከለር (ቀለም) የእይታ ብዥታ ወይም ምናባዊ ነው፡፡